ስለ ህገወጥ ስደተኛ እውነታው
ወደ እንግሊዝ በህገወጥ መንገድ ከመጡ፦
- ህይወትዎን ሊያጡ ይችላሉ። በርካታ ሰዎች በእነዚህ ከመጠን በላይ በተጨናነቁ ጀልባዎች ሲጓጓዙ ሰጥመዋል፣ በመጫጫን ወይም በቅዝቃዜ ሞተዋል። ህገወጥ ስደት ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች ተጨማሪ ይወቁ።
- ወንጀል ይፈጽማሉ። ወደ እንግሊዝ በህገወጥ መንገድ መምጣት ወንጀል ነው።
- ሥራ መስራት አይፈቀድልዎትም። ህግ ጥሰው እዚህ በህገወጥ መንገድ ሥራ የሚሰሩ ስደተኞች በቁጥጥር ስር ይውላሉ። በህገወጥ መንገድ የተገኘ የሥራ ክፍያ ሊወረስ ይችላል።
- እዚህ የመኖር መብት ከሌለዎት የሚመለሱ ይሆናል። ከአሁን በፊት ከነበረው ጊዜ ሁሉ አሁን ተጨማሪ ሰዎችን እየመለስን ነው። በትክክል ስደተኛ የሆኑ ሰዎች ብቻ የሚያስፈልጋቸው ጥበቃ ይደረግላቸዋል።
- በጀልባዎች በህገወጥ መንገድ ወደ እንግሊዝ የሚመጡ ሰዎችን በሙሉ አሁን በቀጥታ እየመለስን ነው። ይህ ማለት፣ እርስዎን ከጀልባ ላይ ማውረድ፣ በቁጥጥር ስር ማዋል እና በቀጣዩ በረራ መመለስ ማለት ነው። የእንግሊዝ እና የፈረንሳይ ስምምነትን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ያግኙ።
ከለላ ያገኙ ቢሆንም፣ ጊዜያዊ እና የተገደበ ብቻ ይሆናል፣ ቪዛ ካላገኙ በስተቀር፦
- ከዚያ በኋላ በቀጥታ ቤተሰብዎን የማምጣት መብት አይኖርዎትም። ጥብቅ መስፈርቶች ተፈጻሚ የሚሆኑ ሲሆን፣ ከሚያስቡት በላይ በጣም ከፍተኛ ወጪ ያለው ሊሆን ይችላል።
- እስከቻሉ ድረስ ለመኖር የምያስፈልግዎትን ወጪ እንዲሸፍኑ ይጠበቃል፣ ያንን ለማድረግም ጠቃሚ ንብረቶችዎን መሸጥ ሊኖርብዎትም ይችላል።
እንግሊዝ በአውሮፓ ውስጥ በጣም ጥብቅ የሆኑ ስደትን የሚመለከቱ ህጎችን ተግባራዊ እያደረገች ነው።
በህገወጥ መንገድ ሥራ ከሰሩ፣ ይታሰራሉ። እዚህ ለመኖር መብት ከሌለዎት፣ ይመለሳሉ።
በአስርት አመት ውስጥ የተመላሽ መጠን ከፍተኛው ደረጃ ላይ ደርሷል።
ጉዞ ሲጀምሩ ከነበረዎት ገንዘብ ያነሰ ገንዘብ ይዘው ሊመለሱ ይችላሉ። ለህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ለመክፈል ገንዘብ ተበድረው ከነበረ፣ መልሰው መክፈል የማይችሉት እዳ ውስጥ ራስዎን ሊያገኙ ይችላሉ።
ህገወጥ ስደተኞች እንግሊዝ ውስጥ ችግር ላይ ይወድቃሉ።
እንግሊዝ ውስጥ እንደ ህገወጥ ስደተኛ ህይወት በጣም አስጀጋሪ ነው።
ወደዚህ በህገወጥ መንገድ ከመጡ፣ ሥራ መስራት አይፈቀድልዎትም። ይህ በህግ የማይፈቀድ አና ጥብቅ ክትትል የሚደረግበት ነው። ህገወጥ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ሊውሉ እና ያገኙት ደመወዝም ሊወረስ ይችላል። አሰሪዎች እርስዎ ሥራ ለመስራት መብት እንዳለዎት ፍተሻ ያደርጋሉ፣ እንዲሁም እርስዎን በህገወጥ መንገድ ሥራ ቢያሰሩ ቅጣት ሊጣልባቸው ወይም ክስ ሊመሰረትባቸው ይችላል።
የሚኖሩበት ቦታ ለማግኘት ሊቸገሩ ይችላሉ። ቤተሰብዎን በቀጥታ ወደ እንግሊዝ ማምጣት አይችሉም።
ሥራ እንደሚያገኙ በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተስፋ ተሰጥቶዎት ከሆነ፣ ውሸት ነው። እነዚህ ወንጀለኞች እርስዎ ያልከፈሏቸው እዳ እንዳለብዎት ከወሰኑ፣ እርስዎን ባሪያ ሊያደርጉዎት ይችላሉ። ህገወጥ ስደት ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች ተጨማሪ ይወቁ።
በርካታ ህገወጥ ስደተኞች ትተው ለመሄድ ይወስናሉ።
ለመሻገር የቻሉ በርካታ ሰዎች ትተው ለመሄድ ወስነዋል። ሌሎቹ ደግሞ መሸወዳቸውን ለማመን በማፈር እየተሰቃዩ ነው።

ምንም አላገኘንም። ጓደኞቻችን እና ጎረቤቶቻችን ምን እንደገጠመን ለማመን ይቸገራሉ። በውጭ ሀገር መስራት ምንም አዋጪ አይደለም። ወደ እንግሊዝ ለመምጣት የተበደርነው የገንዘብ ብድር አሁንም ድረስ አልተከፈለም።

ወደ እንግሊዝ በጀልባ ለመምጣት ተመሳሳይ ውሳኔ አልወስንም። ሀገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቼን እየዋሸኋቸው ነበር። አሁም እዳ ውስጥ ነኝ፣ በቤተሰብ ውስጥ የነበረኝን ክብር እና ተሰሚነት አጥቻለሁ።
ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪን ይጠቁሙ
ቪዛ ሳይኖርዎ ወደ እንግሊዝ እንደሚመጡ ተስፋ የሚሰጥዎት ሰው ካለ፣ ጥቆማ ማድረግ አለብዎት።
እነርሱ ስለ የእርስዎ ደህንነት ወይም የወደፊት ህይወት ደንታ የላቸውም። በእንግሊዝ ሰርጦች በአደገኛ ጀልባዎች ላይ ለሚሞቱ ሰዎች ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተጠያቂ ናቸው።
ያስቁሟቸው። እነርሱን ለእኛ ይጠቁሙ። ማንነትዎ በጥብቅ ሚስጥር ይያዛል።
ህጋዊ ጉዞ
ለተሻለ ህይወት ወይም ደህንነትዎን ለመጠበቅ ወደ እንግሊዝ ለመምጣት ከፈለጉ፣ ወደዚህ መምጣት የሚችሉበት ብቸኛው መንገድ ህጋዊ መስመሩ ነው።