Skip to main content

Facts on UK immigration

በእንግሊዝ እና በፈረንሳይ መካከል የተደረገ አዲስ ስምምነት አለ።

በህገወጥ መንገድ ወደ እንግሊዝ በትንሽ ጀልባ ከመጡ፣ በግዴታ ወደመጡበት ሀገር የመመለስ ችግር ውስጥ ይገባሉ እንዲሁም ወደ እንግሊዝ በድጋሚ ለመግባትም ሆነ ህጋዊ መብት ሳይኖርዎ በፈረንሳይ ውስጥ መቆየት አይፈቀድልዎትም።

በህገወጥ መንገድ ወደ እንግሊዝ በትንሽ ጀልባ ለመምጣት ከሞከሩ፣ ሁሉንም ነገር ሊያጡ ይችላሉ።

ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ደህንነትዎ ተጠብቆ እንግሊዝ እንደሚያደርሱዎት እና እዚያም መቆየት እንደሚፈቀድልዎ ይነግሩዎታል። እየዋሹዎት ነው።

በአዲሱ ስምነት መሰረት፣ በግዴታ ወደመጡበት ሀገር የመመለስ ችግር ውስጥ ይገባሉ እንዲሁም ወደ እንግሊዝ በድጋሚ መግባት አይችሉም። ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ገንዘብዎን ወስደውት ይቀራሉ።

በጣም በርካታ ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች ከመጠን በላይ በተጨናነቁ ጀልባዎች ወደ እንግሊዝ ለመድረስ ሲሞክሩ ሞተዋል። አሁን ከመቸውም ጊዜ በላይ በጣም አደገኛ ሆኗል።

በህገወጥ መንገድ ወደ እንግሊዝ ለመግባት መሞከር በፍጹም አዋጪ አይደለም። በቁጥጥር ስር መዋል እና ከእንግሊዝ እንዲወጡ መገደድ ያጋጥምዎታል።

የወንጀል እንቅስቃሴ ታሪክ ከነበረዎት ወይም ስለ ማንነትዎ እዋሹ ከሆነ፣ ማንነትዎን ለማወቅ እና በእርስዎ ላይ እርምጃ ለመውሰድ በእኛ መረጃ ቋት ውስጥ የማመሳሰል ስራ የምንሰራባቸው የጣት አሻራዎችዎን እና የፊትዎን ምስሎች የምንወስድ መሆኑን ማወቅ ይኖርብዎታል።

ህይወትዎን ለአደጋ አያጋልጡ ወይም ገንዘብዎን አያባክኑ።