Skip to main content

ወደ እንግሊዝ በህገወጥ መንገድ መግባት ከመቸውም ጊዜ የበለጠ አደገኛ ነው።

በትንሽ ጀልባ ላይ ሊሞቱ ይችላሉ።

ወደ እንግሊዝ በትንሽ ጀልባ መምጣት የበለጠ አደገኛ ሆኗል።

ጀልባዎቹ ከመጠን በላይ ሰው ይጭናሉ፣ ለባህር ላይ ጉዞ ብቁ አይደሉም እናም በጉዞ ላይ ይሰባበራሉ።

ወደ ባህሩ ከወደቁ፣ በደቂቃዎች ውስጥ ይሰምጣሉ ወይም ልክ እንደበረዶ ይቀዘቅዛሉ። ለውሸት የሚሰጥዎት የህይወት አድን ጃኬት አያተርፍዎትም።

ነዳጅ በሰውነትዎ ላይ ከተረጨ፣ ቆዳወን ሰርስሮ ያቃጥልዎታል። በዘላቂነት ጠባሳ ወይም የአካል መጎዳት ሊገጥምዎት ይችላል።

ሰዎች በእነዚህ ከልክ በላይ በተጨናነቁ ጀልባዎች ላይ በመረጋገጥ እና በመጫጫን ይሞታሉ።

ብዙ ህጻናት በዚህ መልኩ ሞተዋል። በጀልባ ላይ በመሳፈር፣ ሌላ ሰው ሊገድሉ ይችላሉ–ህፃናትን ጨምሮ።

በትንሽ ጀልባ ላይ በነበሩ ጊዜ ሌላ ሰው ላይ ለሚያደርሱት ጉዳት እስር ይገጥምዎታል።

የወንጀል ጥሰት በመሆኑ እስከ ስድስት ዓመት እስራት ሊያጋጥምዎ ይችላል።

ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ስለ እርስዎ ግድ የላቸውም። እነርሱ የሚፈልጉት ገንዘብዎን ብቻ ነው።

ለዚያም ነው ተጨማሪ ሰዎችን በሀይል ወደእነዚህ ጀልባዎች የሚጭኑት፣ ሰዎች ለመሳፈር ፈቃደኛ ካልሆኑ በመሳሪያ በማስፈራራት ጭምር።

አንዳንድ ጊዜ እርስዎን ያጭበረብራሉ፣ ለእርስዎ ምንም ነገር ሳያበረክቱ ገንዘብዎን ይወስዳሉ።

ገንዘብዎን ወይም ህይወትዎን አደጋ ላይ አይጣሉ።

በጭነት መኪና ውስጥ ሊሞቱ ይችላሉ።

image of people in a lorry

በ2021፣ እንግሊዝ ውስጥ 39 ስደተኞች በጭነት መኪና ተሳቢ ውስጥ ሞተው ተገኝተዋል።

ከውስጥ ታፍነው፣ መተንፈስ አይችሉም ነበር።

በመጨረሻ መልዕክታቸው፣ ከተጎጂዎች አንዱ ‘ወደቤተሰቤ መመለስ እፈልጋለሁ’ የሚል መልዕክት አስቀምጠዋል።

በጭነት መኪና ወደ እንግሊዝ መምጣት በጣም አደገኛ ነው። ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ስለ እርስዎ ወይም ስለሚወዷቸው ሰዎች አይጨነቁም።

ብዙ ጊዜ በሮቹ ከውጭ የሚቆለፉ ናቸው። በፍጹም ጨለማ ውስጥ በከፍተኛ ሙቀት ወይም በከፍተኛ ቅዝቃዜ ሊታፈኑ ይችላሉ።

ብዙ የጭነት መኪና ኮንቴነሮች አየር የማያስገቡ ናቸው። ህገወጥ የሰው አዘዋዋሪው በማንኛውም ምክንያት በሩን መክፈት ካልቻለ ወይም ከባድ የትራፊክ መጨናነቅ በመኖሩ ጉዞው የተራዘመ ጊዜ ከወሰደ፣ ከውስጥ አየር ሊያጥርዎ እና ሊታፈኑ ይችላሉ።

በእርስዎ ወይም በሚወዱት ሰው ላይ ይህ እንዲፈጠር አይፍቀዱ።

ተሳክቶ ቢደርሱ እንኳን፣ አሁንም አደጋ ላይ ነዎት።.

ወደዚህ ጉዞዎን ያመቻቹት ሰዎች ወንጀለኞች ናቸው። ለእነዚህ ሰዎች እዳ ውስጥ መግባት የለብዎትም።

ሥራ እንደሚያገኙ በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተስፋ ተሰጥቶዎት ከሆነ፣ ውሸት ነው።

እነርሱ ጋ ሲደርሱ፣ የእነርሱ ባሪያ ሊሆኑ ይችላሉ። መጠቀሚያ ሊያደርጉዎት እና ሃይል የሚጠቀሙ ሊሆኑ ይችላሉ።

በአነስተኛ ክፍያ ወይም በነፃ ለእነዚህ ወንጀለኞች ሥራ እንዲሰሩ ሊገደዱ ይችላሉ። በእዳ ውስጥ ሆነው፣ ያለምንም መውጫ መንገድ ሊታፈኑ ይችላሉ።

ቤተሰብዎን አደጋ ላይ ሊጥሉ ይችላሉ። ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች እርስዎን በቁጥጥራቸው ስር ለማቆየት ብዙ ጊዜ ከመጡበት ሀገር የሚገኙ ቤተሰብዎን ያስፈራራሉ።

እንግሊዝ ውስጥ እንደ ህገወጥ ስደተኛ ህይወት እጅግ አስቸጋሪ ነው። ህገወጥ ስደትን በተመለከተ ተጨማሪ እውነታዎችን ይወቁ።.

ህገወጥ ስደት ሁልጊዜም ቢሆን ካለው አድጋ ጋር ተመጣጣኝ አይደለም።

ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪን ይጠቁሙ

ቪዛ ሳይኖርዎ ወደ እንግሊዝ እንደሚመጡ ተስፋ የሚሰጥዎት ሰው ካለ፣ ጥቆማ ማድረግ አለብዎት።

እነርሱ ስለ የእርስዎ ደህንነት ወይም የወደፊት ህይወት ደንታ የላቸውም። በእንግሊዝ ሰርጦች በአደገኛ ጀልባዎች ላይ ለሚሞቱ ሰዎች ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተጠያቂ ናቸው።

ያስቁሟቸው። እነርሱን ለእኛ ይጠቁሙ። ማንነትዎ በጥብቅ ሚስጥር ይያዛል።

ህጋዊ ጉዞ

ለተሻለ ህይወት ወይም ደህንነትዎን ለመጠበቅ ወደ እንግሊዝ ለመምጣት ከፈለጉ፣ ወደዚህ መምጣት የሚችሉበት ብቸኛው መንገድ ህጋዊ መስመሩ ነው።