Skip to main content

Privacy Notice

ይህ ድረገጽ የቀረበው በHome Office ከGovernment Digital Service (GDS) ጋር በመተባበር፣ የCabinet Office አካል ሆኖ ነው።

Home Office ናይ እዚ መርበብ ሓበሬታ ዝተሓተተ ዝኾነ ኩሉ ውልቃዊ ሓበሬታን ብኩኪታት ዝተኣከበ ዝኾነ ኩሉ ውልቃዊ ሓበሬታን ተቆጻጻሪ ሓበሬታ እዩ።

Cabinet Office እንደ IP አድራሻዎች የመሳሰሉ የመሰረተ ስርዓት አካል ሆነው የሚቀናበሩ የግል መረጃዎች ውሂብ ተቆጣጣሪ ነው። 

ውሂብ ተቆጣጣሪ የግል መረጃ እንዴት እና ለምን እንደሚቀናበር ይወስናል። ለተጨማሪ መረጃ፣ በበውሂብ ጥበቃ ይፋዊ ምዝገባ ውስጥ የCabinet Office ግብዓትን ያንብቡ።

ምን ውሂብ እንደምንሰበስብ እና ለምን እንደምንፈልገው

ይህን ድረገጽ ሲጎበኙ GDS የተወሰነ ውሂብ በራሱ ይሰበስባል። ይህም የእርስዎን Internet Protocol (IP) አድራሻ፣ እንዲሁም የሚጠቀሙበትን ድር አሳሽ ስሪት ዝርዝር ያካትታል። GDS ይህን መረጃ እርስዎ ለድረገጹ መዳረሻ እንዲኖርዎት ለማስቻል እና የደህንነት ስጋቶችን ለመለየት የድረገጹን አጠቃቀም ለመቆጣጠር ይጠቀምበታል።

እርስዎ ይህን ድረገጽ እንዴት እንደሚጠቀሙበት ለማወቅ የሚከተሉትን መረጃዎች Home Office በGoogle Analytics ወይም በGoogle Analytics 4 መረጃ እንዲሰበስብ ፈቃድዎን ሲሰጡ፦ 

  • GOV.UK ላይ እርስዎ የጎበኟቸው ገጾች
  • በእያንዳንዱ GOV.UK ገጽ ላይ ምን ያህል ጊዜ እንዳሳለፉ
  • ወደ ደረገጹ እንዴት እንደመጡ
  • ድረገጹን በሚጎበኙ ጊዜ ምን ላይ ጠቅ እንዳደረጉ
  • ማንነትዎን በማይገልጽ መንገድ የእርስዎን IP አድራሻ በመጠቀም አጠቃላይ የመገኛ አካባቢዎ ማሳያ።

Google Analytics ወይም Google Analytics 4 በመጠቀም በቀጥታ ማንነትን የሚገልጽ መረጃ (ለምሳሌ ስምዎ ወይም አድራሻዎ) አይሰበሰብም። Home Office የትንታኔ መረጃ በመጠቀም የእርስዎን ማንነት አይለይም እንዲሁም የእርስዎን ማንነት በሚያሳውቅ መልኩ የትንታኔ መረጃ ከሌሎች የውሂብ ስብስቦች ጋር አያጣምርም።

የCloudflare Web Analytics የተቀላቀለ፣ ማንነትን የማይገልጽ የአጠቃቀም ስታቲስቲክስ ብቻ ለመሰብሰብ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን የግል ውሂብ አይሰበስብም ወይም አያቀነባብርም።

Home Office ይህን መረጃ የሚጠቀመው ድረገጹ የተጠቃሚዎቹን ፍላጎት እንደሚያሟላ ለማረጋገጥ እና ማሻሻያዎችን ለማድረግ ነው። 

በዚህ ድረገጽ ላይ ጥቅም ላይ የሚውሉ ኩኪዎችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኩኪዎች ገጽን ይመልከቱ። 

ውሂብዎን በቅንብር ውስጥ ለማሳለፍ ያለው የህግ መነሻ

ከድረገጽ ደህንነት ጋር በተያያዘ የግል ውሂብን በቅንብር ውስጥ ለማሳለፍ የGDS የህግ መነሻ የመሰረተ ስርዓቱን ደህንነት እና ተዓማኒነት ለማረጋገጥ ካለው ተገቢ ፍላጎት የሚመነጭ ነው።

ሌሎች የግለሰብ ውሂቦችን በቅንብር ውስጥ ለማሳለፍ GDS ያለው የህግ መነሻ የሚመነጨው አንድን ተግባር ለማህበረሰብ በሚጠቅም መልኩ ለማከናወን ወይም እንደ አንድ የመንግስት የስራ ክፍል ተግባሮቻችንን ለማከናወን አስፈላጊ በመሆኑ ነው።

Google Analytics ወይም Google Analytics 4 በመጠቀም Home Office የእርስዎን መረጃ ለመሰብሰብ የሚያበቃው ህጋዊ መነሻ የሚመነጨው ከእርስዎ ፈቃደኝነት ነው።

በእርስዎ ውሂብ ምን እንሰራለን

GDS ወይም Home Office አግባብነት ያለው እና ምክንያታዊ ማብራሪያ ሊቀርብበት የሚችል የስራ ፍላጎት በሚኖር ጊዜ የእርስዎን ውሂብ ለሌሎች የመንግስት ሥራ ክፍሎች፣ ኤጀንሲዎች እና የማህበረሰብ አካላት ሊያጋራ ይችላል። በተጨማሪም እንደ ውሂብ አቀናባሪ የሚሰሩ የማስተናገድ አገልግሎት አቅራቢዎች ለመሳሰሉ የቴክኖሎጂ አገልግሎት አቅራቢዎች ውሂብ ሊጋራ ይችላል።

እኛ የማንፈጽማቸው ነገሮች፦

  • የእርስዎን ውሂብ ለሦስተኛ ወገኖች መሸጥ ወይም ማከራየት
  • የእርስዎን ውሂብ ለማሻሻጥ ተግባራት ለሦስተኛ ወገኖች ማጋራት
  • የትንታኔ ውሂብ ግለሰቦችን ለመለየት መጠቀም፣ ማለትም ከሌሎች የውሂብ ነጥቦች ጋር በማገናኘት

ያንን እንድናደርግ በህግ የምንገደድ ከሆነ የእርስዎን ውሂብ እናጋራለን – ለምሳሌ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወይም ማጭበርበርን ወይም ወንጀልን ለመከላከል።

የእርስዎን ውሂብ ለምን ያህል ጊዜ እንደምናስቀምጥ

በዚህ ሰነድ ላይ ለተገለጸው አላማ ውሂቡን ማቆየት አስፈላጊ ለሆነበት ጊዜ ወይም እኛ በህግ ለምንገደድበት ጊዜ ያህል ብቻ የእርስዎን የግል ውሂብ እናስቀምጣለን።

GDS የመዳረሻ ምዝገባ ውሂብ ከ120 ቀናት በኋላ ይሰርዛል። 

Home Office የGoogle Analytics ወይም የGoogle Analytics 4 ውሂብ ከ14 ወራት በኋላ ይሰርዛል።

የልጆች ግላዊነት ጥበቃ

ይህ ድረገጽ 13 ዓመት እና ከዚያ በታች ለሆኑ ልጆች ታስቦ የተሰራ ወይም በማወቅ እነርሱን ዒላማ የሚያደርግ አይደለም። GDS ሆነ Home Office፣ ከ13 ዓመት በታች የሆነን የማንኛውንም ሰው ውሂብ ሆን ብለው አይሰበስቡም ወይም አይዙም።

የእርስዎ ውሂብ የት እንደሚቀናበር እና እንደሚቀመጥ

ከመነሻ መሰረተ ስርዓት ጋር የተያያዘ ውሂብ የሚቀናበረው እና የሚቀመጠው በአውሮፓ የኢኮኖሚ ቀጠና (EEA) ውስጥ ነው። በGoogle Analytics ወይም በGoogle Analytics 4 የሚሰበሰብ ማንኛውም ውሂብ ከEEA ውጭ ወደሆነ አካባቢ ለቅንብር ሊዘዋወር ይችላል። 

ለውሂብዎን እንዴት ጥበቃ እንደምናደርግ እና እንዴት ደህንነቱን እንደምንጠብቅ

የእርስዎ ውሂብ ደህንነቱ የተተጠበቀ እንዲሆን የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን። የእርስዎ ውሂብ ያለፈቃድ እንዳይገኝ ወይም እንዳይታይ ለማድረግ ስርዓቶችን እና ሂደቶችን አዋቅረናል  – ለምሳሌ፣ የተለያዩ ደረጃዎች ያሏቸው ምስጠራዎችን በመጠቀም ውሂብዎን እንጠብቃለን።

በተጨማሪም፣ ከእኛ ጋር የስራ ግንኙነት ያለው ማንኛውም ሦስተኛ አካል እኛን በመወከል የእርስዎን ውሂብ በሚያቀናብር ጊዜ የደህንነት ጥበቃ የሚያደርግ መሆኑን እናረጋግጣለን።

የእርስዎ መብቶች

የሚከተሉትን የመጠየቅ መብቶች አሉዎት፦

  • የእርስዎ የግል ውሂብ እንዴት እንደሚቀናበር የሚገልጽ መረጃ
  • የዚያ የግል ውሂብ ቅጂ
  • በግል ውሂብዎ ላይ ትክክል ያልሆነ ነገር ቢኖር ወዲያውኑ እንዲስተካከል

በተጨማሪም የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦

  • የእርስዎ የግል ውሂብ እንዴት እንደሚቀናበር ቅሬታ ማንሳት
  • የግል ውሂብዎ እንዲቆይ የሚያስገድድ በቂ ምክንያት ከሌለ እንዲሰረዝ መጠየቅ
  • የግል ውሂብዎ ቅንብር በተወሰኑ ሁኔታዎች ገደብ እንዲደረግበት መጠየቅ

ከነዚህ ጥያቄዎች መካከል ማናቸውንም መጠየቅ ቢፈልጉ፣ በኢሜይል gds-privacy-office@digital.cabinet-office.gov.uk መላክ ይችላሉ።

ያነጋግሩን ወይም ቅሬታ ያቅርቡ

ለሚከተሉት ጉዳዮች የGDS የግላዊነት ቡድድንን በ gds-privacy-office@digital.cabinet-office.gov.uk ማግኘት ይችላሉ፦

  • በዚህ የግላዊነት ማሳወቂያ ላይ ጥያቄ ካለዎት
  • የግል ውሂብዎ ያለአግባብ ጥቅም ላይ ውሎ ወይም ያለአግባብ ተስተናግዶ እንደሆነ ካሰቡ

በተጨማሪም የCabinet Office እና የHome Office የውሂብ ጥበቃ ባለሙያዎችን (DPO) በሚከተለው አድራጃ ማግኘት ይችላሉ፦

Data Protection Officer
DPO@cabinetoffice.gov.uk
Cabinet Office
70 Whitehall
London
SW1A 2AS

Office of the DPO
dpo@homeoffice.gov.uk
Peel Building
2 Marsham Street
London
SW1P 4DF

DPOዎች የእኛን የግል መረጃ አጠቃቀም በተመለከተ ገለልተኛ የሆነ የምክር ወይም የቁጥጥር ሥራ ይሰራሉ።

በተጨማሪም፣ ገለልተኛ ተቆጣጣሪ ለሆነ ለInformation Commissioner ቅሬታ ማስገባት ይችላሉ።

Information Commissioner
casework@ico.org.uk

ስልክ ቁጥር፦ 0303 123 1113
የጽሁፍ መልዕክት ስልክ፦ 01625 545860
ከሰኞ እስከ አርብ፣ 9ኤኤም እስከ 4:30ፒኤም
የስልክ ጥሪ ወጪዎችን ለማወቅ

Information Commissioner’s Office
Wycliffe House
Water Lane
Wilmslow
Cheshire SK9 5AF

በዚህ ማሳወቂያ ላይ የሚደረጉ ለውጦች

ይህ ማሳወቂያ ከጊዜ ጊዜ ሊቀየር ይችላል። ይህ በሚሆንበት ሁኔታ፣ በዚህ ገጽ ግርጌ «ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው» በሚል የሚጠቀሰው ቀን ይቀየራል። በዚህ የግላዊነት ማሳወቂያ ላይ የሚኖሩ ማናቸውም ለውጦች በእርስዎ እና በውሂብዎ ላይ ወዲያውኑ ተፈጻሚ ይሆናሉ።

እነዚህ ለውጦች የእርስዎ የግል ውሂብ በሚቀናበርበት ሂደት ላይ ተጽዕኖ ካላቸው፣ GDS እና Home Office እርስዎን ለማሳወቅ ምክንያታዊ የሆኑ እርምጃዎችን ይወስዳሉ።

ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው 11 ግንቦት 2026